|
|
|||
|
||||
Overviewመንፈሳዊ ሕይወት ጉዞ ነው፤ ከአንድ የአመለካከት፣ የሕይወት፣ የባሕሪ፣ የአቅም፣ የብስለት የራእይ ደረጃ ወደ ሌላ የአመለካከት፣ የሕይወት፣ የባሕሪ፣ የአቅም፣ የብስለትና የራእይ ደረጃ የሚደረግ ጉዞ። ለዚህ ዓይነቱ ጉዞ ቀጥተኛ ምሳሌ እንዲሆነን እግዚአብሔር ዘጸአት የተባለ የዕብራውያንን የጉዞ ዘገባ የያዘ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲቀመጥልን አድርጓል። በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ውስጥ ከሌለን፣ ሕይወታችን ወደ ሃይማኖታዊነት ያሽቆለቁላል። ሕያው የሆነ የክርስትና ሕይወት ይዘት እንዳለን የሚታወቀው በምናደርገው የወደፊት ተራማጅ ግስጋሴ ነው። ጉዞ ካለ እንቅስቃሴ፣ እርምጃ፣ መሻሻል፣ እድገት፣ ተጽዕኖ፣ ግብ ይኖራል። እነዚህ እሴቶች (values) ለሕይወታችን እጀግ አስፈላጊ ቅመሞች ናቸው። ይህ መጽሐፍ የክርስትና ሕይወታችን እንቅስቃሴ፣ መሻሻል፣ እድገት፣ ተጽዕኖና ግብ እንዲኖረው ለማገዝ የተጻፈ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ሕይወት በሌላ ቋንቋ የደቀመዝሙርነት ሕይወት ተብሎ ይታወቃል። የዚህ መጽሐፍ ጽንሰ ሐሳብ የደረጀው በዚህ የደቀመዝሙርነት ሕይወት ጅማሬ፣ ሂደት፣ ተግዳሮትና ግብ ላይ ነው።በዚህ መጽሐፍ የኢየሱስ ክርስቶስን ወላጆችና ደቀመዛሙርት ሕይወት ቀረብ ብለን እንመለከታለን። የእነዚህ ደቀመዛሙርት ሕይወት የደቀመዛሙርትነት ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚያሳየን ብሉ ፕሪንት ነው። ይህንን ብሉ ፕሪንት አገላብጠንና ጠለቅ ብለን ከራሳችን ሕይወት ጋር በማዛመድ ለመመልከት እንሞክራለን። የደቀመዛሙርቱን ሕይወት ስንመለከት በመከተል ውስጥ ያሉትን አንዳንድ አንኳር ነገሮች መገንዘብ ብቻ ሳይሆን፣ የደቀመዛሙርቱን መምህር የበለጠ እያወቅነው እንመጣለን። Full Product DetailsAuthor: Ermias TilahunPublisher: Ermias Woldeyesus Imprint: Ermias Woldeyesus Dimensions: Width: 12.70cm , Height: 0.70cm , Length: 20.30cm Weight: 0.132kg ISBN: 9798349622571Pages: 128 Publication Date: 29 August 2013 Audience: General/trade , General Format: Paperback Publisher's Status: Active Availability: Available To Order We have confirmation that this item is in stock with the supplier. It will be ordered in for you and dispatched immediately. Language: Amharic Table of ContentsReviewsAuthor InformationTab Content 6Author Website:Countries AvailableAll regions |
||||