|
|
|||
|
||||
Overview"መግቢያ ""ኢትዮጵያና መጽሐፍ ቅዱስ"" በሚል ርዕስ በቀረበው በዚህ ጥናት፥ ኢትዮጵያ፥ ለዓለም፥ በቋንቋ፣ በታሪክ እና በአምልኮ ውስጥ የነበራትን ድርሻና ያበረከተችውን አስተዋጽዖ እንመረምራለን። የጥናቱ አላማ፥ ኢትዮጵያውያ፥ ለዓለም ያበረከተቻቸውን መልካም ነገሮችን፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ በመፈለግ፥ ለአንባቢዎች፣ ለተመራማርዎች እና ለጸሐፊዎች፥ ለመነሻ የሚሆኑ ነጥቦችን ማጋራት ነው። በዚህ ጥናት፤ ከአብርሃም ዘመን (2000 ዓመተ ዓለም) እስከ ክርስትና (በመጀመሪያው ዓመተ ምህረት) የነበረውን፥ በኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ክዋኔዎችን፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መርምሮ ማቅረብ ይሆናል። በተለይም፥ ስለ አብርሃም፣ ሙሴ እና ጌታ ኢየሱስ፥ በመጽሐፍ ቅዱስ የቀረበ ቋንቋን፣ ታሪክን እና ስርዓተ አምልኮን ይመረምራል፣ ያብራራል፣ ያልተጻፋ ክፍሎችን ከተጻፋት ጋር በማገናዛብ ለመረዳት እና ለማብራራት ጥረት ይደረጋል። ኢትዮጵያ ለዓለም ህዝቦች፥ ስልጣኔ፣ ሰላም፣ ፍትህ... ወዘተ ያበረከተችውን፥ እና አስተዋጾ ያደረገውን የሚዳስስ፣ የሚመረምርና ተጨባጭ መረጃዎችን ለማሳየት የሚያስችል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥናት ነው። ጥናቱ፥ በአራት ክፍሎች የተከፈለ ነው፥ የመጀመሪያው ክፍል፥ ኢትዮጵያ ከቋንቋ አንጻር፥ ለተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች ያበረከተቸውን፥ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በምሳሌነት በመውሰድ፥ በንጽጽር ለማሳየት ተሞክሯል። ይህም ከዓለም ቋንቋዎች ውስጥ፥ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ቀዳሚ ስለመሆናቸው፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ቀርበውበታል። ለሰዎች፥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሞችን የሰጠ እግዚአብሔር፥ በኢትዮጵያ ስለመሆኑ... እና እግዚአብሔር የሚጠራበትን በመጀመሪያ ያሳወቀው ለኢትዮጵያውያን መሆኑን፤ ለእግዚአብሔርም ስሞችን ያወጡ፥ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው እናያለን። እንዲሁም፥ በዓለም ላይ የሚታወቁ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ የቦታ ስያሜዎች ሁሉ፥ አስቀድሞ በኢትዮጵያው ውስጥ የነበሩ ስሞች መሆናቸውን ለማሳየት ተሞክሯል። የጌታን፣ የመላእክት፣ የነብያት፣ የሐዋርያት፣ የቦታዎች እና የተለያዩ ነገሮች ስሞችን ትርጉም ማወቅ፤ የስሞች ምንጭ (ሥርዎ ቃል)፥ መነሻቸው እና መሰረታቸው የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መሆናቸውን ለመረዳት እንዲያግዝ የሚያደርግ መንገዶችን ይጠቁማል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስሞች፥ ከመጠሪያነት በተጨማሪ፥ ምስጢራዊ መልእክትና መንፈሳዊ ፍች ያላቸው መሆኑን ማወቅ እና ማሳየት መጽሐፍ ቅዱስን እና መንፈሳዊ መልክቱን በጥልቀት ለመረዳት እገዛ ያደርጋል። በጽሑፍም ሆነ በቃል ያሉ መልእክታት፥ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ከቋንቋ ወደ ቋንቋ በተተረጎሙ መጠን፥ ምን ያህል የመጀመሪያ ትርጉማቸውንና መልክታቸውን እየለቀቁ እንደሚሄዱ በመገንዘብ፥ ታሪክ ጸሐፊዎች ትክክለኛውን ድርጊት መዝግበው ለማቆየት እንዲችሉ ያግ" Full Product DetailsAuthor: Markos Desta NPublisher: Independently Published Imprint: Independently Published Dimensions: Width: 14.00cm , Height: 1.90cm , Length: 21.60cm Weight: 0.431kg ISBN: 9798354779703Pages: 340 Publication Date: 18 November 2022 Audience: General/trade , General Format: Paperback Publisher's Status: Active Availability: Temporarily unavailable The supplier advises that this item is temporarily unavailable. It will be ordered for you and placed on backorder. Once it does come back in stock, we will ship it out to you. Table of ContentsReviewsAuthor InformationTab Content 6Author Website:Countries AvailableAll regions |